በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ተጀምሯል።

26
እንጅባራ: ታኅሣሥ 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፖሊዮ የእጅ እና የእግር መስለልን በማስከተል ሕጻናትን ለሞት እና ለዘላቂ የአካል ጉዳት የሚዳርግ በሽታ ነው።
በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሽታው የሚያደርሰውን ጉዳት ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለኾኑ ሕጻናት ክትባት መሰጠት ተጀምሯል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ጤና መምሪያ ኀላፊ አየለ አልማው ፖሊዮ (የልጅነት ልምሻ) መድሃኒት ያልተገኘለት አደገኛ እና ገዳይ በሽታ መኾኑን ተናግረዋል።
በሽታውን ቀድሞ ለመከላከል በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከ206 ሺህ በላይ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የኾኑ ሕጻናትን ተደራሽ የሚያደርግ የተቀናጀ ክትባት መስጠት ተጀምሯልም ነው ያሉት።
ክትባቱ ከታኅሣሥ 3 እሰከ 6/2018 ዓ.ም ድረስ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች እንደሚሰጥም ገልጸዋል።
ቤት ለቤት በሚሰጠው በዚህ ክትባት ወላጆች እና አሳዳጊዎች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ልጆቻቸውን ተከታትለው በማስከተብ ኀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ከዚህ በላይ የግፍ ጽዋ እንዲፈስ መፍቀድ አይገባም” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)
Next articleየመሪዎችን አቅም ወደ ተቋም ግንባታ ማሳደግ የትኩረት አቅጣጫ ነው።