
ደብረ ብርሃን: ታኅሣሥ 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ለደብረ ብርሃን ከተማ እና ለሰሜን ሸዋ ዞን መካከለኛ መሪዎች “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ መልዕክት ሲሰጥ የቆየው 3ኛው ዙር ሥልጠና ተጠናቅቋል።
በግብርና እና ገጠር ትራንስፎርሜሽን፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በከተሜነት እና በቱሪዝም ልማት ጉዳዮች ዙሪያ አቅምን የሚፈጥር ሥልጠና መሰጠቱን የተናገሩት የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሰለሞን ጌታቸው ናቸው።
በሥልጠናው በግብርና እና ገጠር ትራንስፎርሜሽን፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በከተሜነት እና በቱሪዝም ልማት እምርታ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ አቅምን የሚፈጥር ሥልጠና ነው የተሰጠው ብለዋል።
ጸጋዎቻችንን በመለየት ውጤታማ ሥራዎችን መሥራት የሚያስችል ሥልጠና እንደኾነ ነው የገለጹት።
የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ ተክለየስ በለጠ በዞናችን ያለንን የግብርና እና የቱሪዝም አቅምን በተገቢው መንገድ መጠቀም የሚያስችል ሥልጠና ስለመኾኑም ተናግረዋል።
በከተሜነት እና የገጠር ትራንስፎርሜሽን ላይ መሪዎች በትኩረት እንዲሠሩ አቅጣጫ የሰጠ ሥልጠና ሰለመኾኑም ገልጸዋል፡፡
የሥልጠናው ተሳታፊዎች ከሥልጠናው አቅምን የሚያሳድግ ግንዛቤ የጨበጡበት እንደኾነ ተናግረዋል።
ባገኙት ግንዛቤም ማኅበረሰቡን እና ሀገርን የሚጠቅሙ ሥራዎችን ለመሥራት መነሳሳት እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።
ሥልጠናው በቀጣይነት ለታችኛው መዋቅር መሪዎችም ተደራሽ እንደሚኾን በ3ኛው ዙር ሥልጠና ማጠቃለያ ላይ ተመላክቷል::
ዘጋቢ:- ሥነ ጊዮርጊስ ከበደ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
