መሪዎች በየአካባቢው ያሉ እምቅ ሃብቶችን ለይተው ሊያለሙ ይገባል።

5
ፍኖተ ሰላም: ታኅሣሥ 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ”በመደመር መንግሥት እይታ፤ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ መልዕክት ሥልጠና እየወሰዱ ያሉ መካከለኛ መሪዎች በፍኖተ ሰላም ከተማ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን እና በማምረት ላይ የሚገኙ ፋብሪካዎችን ነው የተመለከቱት።
የጉብኝቱ ተሳታፊ መሪዎች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች በጸጥታ ችግርም ውስጥ ኾኖ መሥራት እንደሚቻል ማሳያ መኾናቸውን ገልጸዋል።
በግንባታ ላይ የሚገኘው የፍኖተ ሰላም ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የዞኑን የልማት ተጠቃሚነት ያረጋገጠ እና በርካታ የሰው ኀይልን ለማፍራት ትልቅ አቅም የሚፈጥር እንደኾነ አስረድተዋል።
ከሥልጠናው የተገኙ ግብዓቶችን በመጠቀም በአካባቢያቸው ፕሮጀክቶችን ለማከናወን ትልቅ የቤት ሥራ እንደሰጣቸው አብራርተዋል።
በአንድ በኩል የሰላም ሁኔታውን ማረጋጋት በሌላ በኩል ደግሞ ኅብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚ እንዲኾን እንደሚሠሩም ነው ያረጋገጡት።
በብልጽግና ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ሙላት ጌታቸው ጉብኝቱ መሪዎች ያገኙትን ሥልጠና ወደ ተግባር በመለወጥ የልማት ሥራዎችን እንዲያሰፉ ዓላማ ያደረገ መኾኑን አስገንዝበዋል።
ሰላምን ከማረጋጋት ጎን ለጎን ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑንም አብራርተዋል።
“መሪዎች በየአካባቢው ያሉ እምቅ ሃብቶችን ለይተው ሊያለሙ” ይገባል። ፕሮጀክቶችን እንዲያጠናቅቁም ይጠበቃል ብለዋል። የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ መሪዎች ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል እንደኾነም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየተጠባባቂ ጥሪ ማስታወቂያ
Next articleሕጻናት ክትባት ማግኘት መብታቸው ነው።