
ደብረ ማርቆስ: ታኅሣሥ 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር “በመደመር መንግሥት እይታ፤ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ መልዕክት ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት ለአመራሮች ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና የቀጣይ ተልዕኮዎችን በመስጠት ተጠናቅቋል።
ሥልጠናው በአመራሩ መካከል የሚስተዋሉ የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት ክፍተቶችን በመሙላት የታቀዱ ዘርፎች ግብ እንዲመቱ በትብብር እና በቅንጅት ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ መነሳሳት ያሳየበት መኾኑን በብልጽግና ፓርቲ የደብረ ማርቆስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መልካሙ ሽባባው ገልጸዋል።
የሥልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሥልጠናው ያገኙትን አቅም እና ግብዓት ወደ ተግባር በመለወጥ የተሰጡ ተልዕኮዎችን በአግባቡ ለመወጣት እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ በቴክኖሎጂ የዳበረ እውቀት እና ክህሎት በመላበስ ለወቅቱ የሚመጥን የአመራር ጥበብን በማረጋገጥ የተቀረፁ ሀገራዊ የልማት ዘርፎች ውጤት እንዲያስመዘግቡ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
በቀጣይ ተልዕኮዎችን በመውሰድ ሕዝቡን ለለውጥ የሚያዘጋጅ ታታሪ፣ ታማኝ እና ቁርጠኛ አመራር ኾኖ መገኘት ይገባል ብለዋል።
በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ አመራሮች 3ኛ ዙር ሥልጠና አመራሮች ከንድፈ ሃሳብ እውቀት በተጨማሪ በተግባር ልምድ እና ተሞክሮ ያገኙበት መኾኑ ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
