በእንጅባራ ከተማ ሥልጠናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ መሪዎች የከተማዋን የልማት እንቅስቃሴ ጎበኙ።

6
እንጅባራ: ታኅሣሥ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “በመደመር መንግሥት እይታ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ መልዕክት ከኅዳር 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሥልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ መካከለኛ መሪዎች የእንጅባራ ከተማን የልማት እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
በግንባታ እና በማምረት ሂደት ላይ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ የሌማት ትሩፋት እና ሰው ተኮር የልማት ሥራዎችም ጉብኝት ከተካሄደባቸው ዘርፎች መካከል ይገኙበታል። የጉብኝቱ ተሳታፊዎችም በአምራች ኢንዱስትሪ እና በሌማት ትሩፋት ዘርፎች ተስፋ ሰጭ ጅምሮችን መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በዘርፉ ያጋጠሙ ውስንነቶችን በመፍታት ዘርፉን ከዚህ በላይ ማላቅ ደግሞ ከሠልጣኝ መሪዎች ተጠባቂ ተግባር ነው ብለዋል።
ከጉብኝቱ ያገኙትን ልምድ ከአከባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማስተሳሰር የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሠሩም ሠልጣኞቹ ተናግረዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፍት ቤት ኀላፊ ዓለሙ ሰውነት ጉብኝቱ ሠልጣኞች በንድፈ ሃሳብ የወሰዱትን ሥልጠና መሬት ላይ ካለው የዘርፎች እምርታ ጋር እንዲያስተሳስሩ እና ልምድ እንዲቀሰሙ የሚያስችል መኾኑን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleለሕዝባችን ያመጣነው ለውጥ ባለመኖሩ ወደ ዘላቂ የሰላም ስምምነት መጥተናል” አፋህድ
Next articleየሰላም አማራጭን ለተቀበሉ ታጣቂዎች የተሃድሶ ሥልጠና መስጠት ተጀመረ።