“በዓባይ ጉዳይ የግብጽ አቋም ስህተትና ስግብግብነት የተሞላበት ነው፡፡” ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

679

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 17/2012 ዓ.ም (አብመድ) ኢትዮጵያውያን በዓባይ ዙሪያ የግብጽን የውሸት ትርክት በማጋለጥ እውነታውን ለዓለም ኅብረተሰብ ማሳወቅ እንደሚገባቸው ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ተናግረዋል፡፡

በአባይ ወንዝ እንደ ባለቤት ያጣነውን መብት፣ በአልሲሲ መንግሥት እየተፈጸመ ያለውን ደባና “አባይ የግብጽ የተፈጥሮ (የአላህ) ስጦታ ነው” የሚለውን የውሸት ትርክት ለዓለም አቀፍ ተቋማት መናገርና ማቅረብ የዜግነት ግዴታ መሆኑን ኡስታዝ አቡበከር አስገንዝበዋል፡፡ በዓባይ ጉዳይ የግብጽ አቋም ፍጹም ስህተትና ስግብግብነት የተሞላበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ማንኛውም ዜጋ ያለማንም ቀስቃሽ የሀገሩ አምባሳደር መሆን እንዳለበትና የዜግነት ግዴታው እንደሆነም የጠቆሙት ኡስታዝ አቡበከር በውሸት የፖለቲካ ሴራ የሚያሴሩትን አካላት በተገኘው አጋጣሚ ለዓለም ማኅበረሰብና ተቋማት ማጋለጥ እንደሚያስፈልግ ማስገንዘባቸውንም ኢፕድ ዘግቧል፡፡

ግብጻውያን በዩኒቨርሲቲዎቻቸው የሚገኙ ታላላቅ የእስልምና እምነት አስተማሪዎችን ጭምር የእስልምና መርሆችንና ሕግጋትን ጥሰው ለፖለቲካ ጥቅም ሲሉ “አላህን” ሳይፈሩ እየዋሹ እንዳሉና በኢትዮጵያ ላይ በደል ማድረሳቸውንም በእውነተኛ ማስረጃዎች አስደግፎ ማጋለጥ እንደሚገባ ነው ያስረዱት፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleከ27 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን ሚኒስቴሩ ገለጸ፡፡
Next articleየአብቁተ ባንክ የመሆን ጥያቄ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ፈቃድ ያገኛል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስታወቁ፡፡