በግልፅ በመነጋገር ከተማዋ ወደ ቀደመ ሰላሟ እንድትመለስ እንሠራለን።

6
ደብረ ማርቆስ: ታኅሣሥ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር “ዘካሪ መካሪ ኅብረተሰብ፣ ለዘላቂ ሰላምና ልማት” በሚል መሪ መልዕክት በንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ክፍለ ከተማ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
የሰላም እጦቱ በከተማዋ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አሥተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
ሰላምን ለማረጋገጥ ያሉ ችግሮች በግልፅ በመነጋገር መፍትሔ አመላካች ሃሳቦችን ወደ ፊት በማምጣት ከተማዋ ወደ ቀደመ ሰላሟ እንድትመለስ በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል።
ከተማ አሥተዳደሩም ለማኅበረሰቡ የመሰረተ ልማት ተጠቃሚነት፣ የኑሮ ውድነት ማረጋጋት እና የሥራ እድል ፈጠራ ላይ በትኩረት ሊሠራ ይገባል ነው ያሉት።
በብልጽግና ፓርቲ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መልካሙ ሽባባው የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ለማስቀጠል ማኅበረሰቡ ሰላምን ሊያፀኑ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ በከተማዋ ሰላም ከማስፈን ጎን ለጎን ከተማዋን በሁሉም ዘርፍ የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ይሠራል ነው ያሉት።
በመድረኩ የተገኙት በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዥ ሜጄር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን ማኅበረሰቡ ከፀጥታ ኀይሉ ጎን በመቆም ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በመድረኩ ኅብረተሰቡ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የሚጠበቅበትን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“መታከም ባለመቻሌ እግሬ ተቆርጧል፣ ዓይኔም ማየት አቁሟል” የሰላም እጦቱ ህክምና የነፈጋቸው አባት
Next articleፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለምን ይጠቅማል?