
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 ዓ.ም በመጀመሪያው አራት ወራት የተፈፀመ የመሰረተ ልማት እና የኀይል ስርቆትን አስመልክቶ ጋዘጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫው የተቋሙ ማርኬቲንግ የስኩይቲቭ ዳሬክሬክተር ብርሃኑ ዋቅጅራ በትራንስፎርመር ስርቆት፣ የኤሌክትሪክ አስተላላፊ ኬብል ስርቆት፣ በመኪና ግጭት የደረሰ የመሰረተ ልማት ውድመትን በሚመለከት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በአራት ወራት 17 የትራንስፎርመር ስርቆት፣ የኤሌክተሪክ ኀይል አስተላላፊ ኬብል ስርቆት፣ በመኪና ግጭት እና በኀይል ስርቆት በአጠቃላይ በደረሰው ውድመት እና ስርቆት በአራት ወራት 143 ሚሊዮን 299 ሺህ 114 ነጥብ 93 ብር በተቋሙ ላይ ጉዳት አድርሷል ሲሉም አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።
በተቋሙ በኀይል ስርቆት በመሰረተ ልማት በኬብል ስርቆትና ውድመት የደረሱ ጉዳቶች 107 መኾናቸውን ገልጸው በውድመቱ ላይ 10 የወንጀል ክሶች በመኖራቸው ጉዳዩ በፍርድ ሂደት ላይ ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
