
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 16/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ3 ሺህ 775 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ በ185 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህንን ተከትሎም በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4 ሺህ 848 ደርሷል፡፡
ዛሬ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 184 ኢትዮጵያውያን ናቸው፤ 138 ቫይረሱ የተገኘባቸው ሴቶች ናቸው፡፡ ዕድሜያቸውም ከሦስት ወር ሕጻን እስከ 80 ዓመት አዛውንት እንደሆነም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 160 ሰዎች ከአዲስ አበባ (105 ከውጭ ተመላሾችና በለይ ማቆያ የነበሩ) ናቸው፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ከተለያዩ ክልሎች ናቸው፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት 115 ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 412 ደርሷል፡፡
ኢትዮጵያ አጠቃላይ 223 ሺህ 341 ሰዎችን መርምራ በ4 ሺህ 848 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መኖሩን አረጋግጣለች፤ 3 ሺህ 359 ሰዎች በሕክምና ላይ ናቸው፤ 38 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ክፍል ይገኛሉ፤ የ75 ሰዎች ሕይወት ደግሞ አልፏል፡፡
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡
