
ደሴ፡ ኅዳር 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ የሚካሄደው የሃይማኖት ፎረም ጉባኤ ሰላምን በማፅናት ላይ ያለመ ነው። ይሄን የደገፈ የከተማዋ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍም በተለያዩ መልእክቶች በሆጤ ስታዲየም እየተካሄደ ነው።
ወደ ስታዲየሙ በሚጓዙ ሰልፈኞች ከተላለፉ መልእክቶች መካከልም፦
👉🏻ጦርነት ይብቃ ስላም ይፅና!!
👉🏻ሰላም አንድነትና አብሮነት ከሃይማኖት ተቋም የተቀዱ ናቸው ።
👉🏻የሃይማኖት ተቋማት የሚያደርጉት ውይይት ግጭቶችን ለመፍታት ወሳኝ መሣሪያ ናቸው!
👉🏻ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን የአብሮነታችንና የጥንካሬዎቻችን መሰረቶች ናቸው!!
👉🏻ሃይማኖት የሰላም መሰረት ነው!
👉🏻የሰላምና የመከባበር ባሕልን ለማስቀጠል የሃይማኖት ተቋማት ሚና የማይተካ ነው !
👉🏻ሰላም አንድነትና አብሮነት ከሃይማኖት አባቶች የተቀዱ እሴቶቻችን ናቸው!! የሚሉ ይገኙበታል።
ዘጋቢ:- ሙሐመድ በቀለ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
