
ባሕር ዳር: ሕዳር 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በመደበኛ ጉባኤው ከሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የተወከሉ ጉባኤተኞች የተሳተፉ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጭ ቦርድ ተወካዮች እና ተጋባዥ እንግዶችም ተገኝተዋል።
በመደበኛ ጉባኤው የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔ እንደሚያሳልፍም ይጠበቃል።
በጉባኤተኛው የፓርቲው እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ይቀርባል። ጉባኤተኛው የፓርቲው የደምብ ማሻሻያም ላይ ተወያይቶ የሚያጸድቅ ይሆናል።
በጉባኤው ፓርቲውን ለቀጣይ ሦስት ዓመታት የሚመሩ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ ሥራ አስፈፃሚ አባላት እንዲሁም የፓርቲውን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር እንደሚመርጥ ፓርቲው ለአሚኮ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
