የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች በደቡብ ወሎ ዞን ጊንባ ከተማ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው።

8
ደሴ: ኅዳር 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የተመራ ልዑክ በደቡብ ወሎ ዞን ጊንባ ከተማ አሥተዳደር በወቅታዊ ክልላዊ እና ሀገራዊ የሰላም እና የልማት ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር እየመከሩ ነው።
በምክክሩ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍሰሀ ደሳለኝ፣ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን፣ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አሰፋ ቸኮል እና ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እየተሳተፉ ነው።
በውይይት መድረኩ ከመቅደላ፣ ከተንታ እና ከለጋምቦ ወረዳዎች እንዲሁም ከጊንባ እና ከአቀስታ ከተማ አሥተዳደር የተውጣጡ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ይገኛሉ።
ዘጋቢ፦ ጀማል ይማም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ዘላቂ ሰላም ያለ ጠንካራ የባሕል እሴት ግንባታ ሊረጋገጥ አይችልም” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)
Next articleበአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ።