
ባሕር ዳር: ኅዳር 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በክልሉ ተፈጥሮ የቆየው ግጭት ለክልሉን ሕዝብ ጉስቁልና፣ ለመሠረተ ልማት እና ኢኮኖሚያዊ ውድመት የሚዳርግ በመሆኑ ስምምነቱ አስፈላጊ ነው ሲል ገልጿል።
በስምምነቱ ላይ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል በአብዛኛው ላይ ስምምነት ተደርሷል ብሏል።
የአማራ ክልልም ከግጭት ነጻ እንዲሆን በጋራ በመሥራት እና ዓለማቀፍ ተቋማትም እገዛ እንደሚያደርጉም ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
በግጭት እና ጦርነቱ ማንም አሸናፊ እንደሌለ እና ሕዝብ እና ሀገር የሚጎዳ መሆኑን ያሳየ እንዲሁም ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚቻል ያሳየ ሁነኛ ማሳያነውም ብሏል።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያላትን ብሄራዊ ጥቅም እንዳይከብር ግብጽና ሻዕብያን የመሳሰሉ አካላት እየሰሩ ይገኛሉ። ይህ የሚሆነው ደግሞ ሀገር ውስጥ ባሉ ተገንጣይ ነን በሚሉ አካላት በኩል አጀንዳቸውን እያስፈጸሙ ነው ብሏል።
የአሰብና የቀይ ባሕር ጉዳይ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የሞት ሽረት ጉዳይ እና ከመንግስት ጋር የሀገሪቱን ጥቅም እና የሕዝብ ጥያቄ ለማስከበር የሚሠራበት መሆኑንም ተናግረዋል።
የግል ፍላጎትን ወደ ግል በመተው ሌሎች አካላትም የሀገርን ጥቅም ለማስከበር መስራት እንዳለባቸው ጥሪም አቅርቧል።
ህወሃትና ሻእቢያ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ዓመታት ሰርተዋል አሁንም የትግራይ ምድርን እያተራመሱ ይገኛሉ። ነገርግን ችግሮችን ከጠመንጃ ይልቅ በውይይት ለመፍታት ቅዲሚያ ሊሰጣ እንደሚገባም አንስተዋል።
ሁለቱ ኃይሎች ከትግራይ ምድር በተጨማሪ በመላው ኢትዮጵያ በሃይማኖትና ብሄር ሰበብ ትርምስ ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን አስረድተው በጋራ መቅረፍ አለብንም ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
