የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ሆሳዕና ከተማ ገቡ።

10

አዲስ አበባ: ኅዳር 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር 20ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀንን ለማክበር ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ገብተዋል።

ሆሳዕና ከተማ ሲገቡም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ.ር)፣ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃድያ ብሔር ተወካዮች፣ የክልሉ የባሕል ቡድን እና ማርሽ ባንድ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዘጋቢ: ኢብራሒም ሙሐመድ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሞሰብ አንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት እየታየ ነው።
Next article“ባለን ጸጋ እንዳንጠቀም እንቅፋት በዝቷል” አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ