ባለፈው ዓመት ሕይወታቸው ያለፉ የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።

280

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 15/2012 ዓ.ም (አብመድ) በሥነ ሥርዓቱ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ሰኔ 15 በክልሉ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ሕይወታቸውን ላጡ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የፀጥታ ኃይሎች መታሰቢያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው። በርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ግቢ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተጀምሯል፡፡ ለመሪዎቹ የመተሰቢየ ሃውልት መሠረትም ተቀምጧል፡፡

የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ዝክረ ሰማዕታት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብርም እየሄዱ ነው።

በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የክልሉ ምክር ቤት አፊ ጉባኤ ወርቅ ሰሞ ማሞ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ችግኝ ተክለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዷል፤ በአማራ ክልል ደግሞ 1 ነጥብ 75 ቢሊዮን ችግኝ የመትከል ሥራው ተጀምሯል፡፡

ከእነዚህም 165 ሚሊዮን ችግኞች በአማራ ክልል ከተሞች የመትከል መርሀ ግብር መያዙ ይታወሳል።

ዘጋቢ፦ ኪሩቤል ተሾመ

Previous article‘‘ግብፆች የሦስቱ ሀገራት ድርድር ቴክኒካል ጉዳይ መሆኑን ቢያውቁም የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ አቅጣጫ ለማላበስ ነው የሚጥሩት፡፡’’ አቶ ፈቅ አህመድ ነጋሽ
Next articleየመከላከያ ሠራዊት ግንባታ ስትራቴጂ ሰነድ ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ተቀባይነቷ እንዲጨምር በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱን ዶክተር ዐብይ አህመድ አስታወቁ።