የደቡብ ጎንደር ዞን ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል እየሠራ ነው።

11

ደብረ ታቦር: ኅዳር 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ጎንደር ዞን ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ላይ ያተኮረ መድረክ አካሂዷል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ቀርቧል። አስገዳጆ ፍልሰት ተፈጥሯዊ በኾነ ምንክያት፣ በግጭት እና በጦርነት፣ የተሻለ ሕይወት ለመምራት ሰዎች ስደትን ሲመርጡ ይስተዋላል ነው የተባለው።

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር በዓለም ከአደንዛዥ እፅ እና ከሕገወጥ የመሳሪያ ዝውውር ቀጥሎ በሦስተኛ ደረጃ የሚገኝ አስከፊ የወንጀል ድርጊት መኾኑ ተጠቅሷል።

የውይይቱ ተሣታፊ ሙሉእመቤት ግዳፌ ስለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የተሠጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ጥሩ እንደኾነ ገልጸው ይህን እድል ሌሎች እህቶች እና ወንድሞች ቢያገኙት መልካም ነው ብለዋል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መፈጠሩ አስፈላጊ ነው ያሉት የዞኑ ፍትሕ መምሪያ የወንጀል የሥራ ሂደት አሥተባባሪ አሠፋ ጫኔ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር በተደራጀ ኀይል የሚፈፀም ነው፤ ይህን ደግሞ ከፍትሕ አካላት ጋር በቅብብሎሽ መሥራት አለብን ነው ያሉት።

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ለፍትሕ አካላት የሚተው ብቻ አይደለም የሁሉም ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል። የዞኑ የሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ የሴቶችና ሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኛ እና የአረጋውያን ማካተት እና ተጠቃሚነት ቡድን መሪ ሃመልማል ማዘንጊያ ለስደት እና እንግልት ጠርፍ እና ድንበር አቋርጠው የሚሄዱበት ምክንያት የሥራ ፈላጊ ቁጥር መጨመር ስለመኾንም አክለዋል።

በደላሎች ስር የሰደደ ተግባር ለመግታት ሁሉም በየደረጃው ያሉ አካላት አጀንዳ አድርጎ እንዲይዝ የሚያስችል የግንዛቤ ፈጠራ መከናወን ትልቅ ጉዳይ ነው ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበየደረጃው የሚገኝ የፖሊስ መሪ እና አባል በንጽሕና ለሕዝቡ አገልግሎት የሚሰጥ መኾን አለበት።
Next articleወጣቶች የችግሮች የመፍትሔ አካል ሊኾኑ ይገባል።