
ደብረ ብርሃን: ኅዳር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አካላት፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላት እና የተለያዩ የክልል አፈ ጉባኤዎች በደብረ ብረሃን ከተማ የሞዴል ቀበሌን እና የጠርሙስ ፋብሪካን ጎብኝተዋል፡፡
የአማር ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ “ደብረ ብርሃን ከተማ የአልሚዎችን እና አምራች ኢንድስትሪዎችን ቀልብ እየሳበች የምትገኝ ከተማ ናት” ብለዋል።
የኢንቨስትመንት መስፋፋት ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ከፍ እንዲል እያደረገ መኾኑን ተገንዝበናል ብለዋል፡፡ ለዚህም የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች የእንግዳ ተቀባይነት ትልቅ ድርሻ አለው ነው ያሉት።
ኅብረተሰቡ ለኢንቨስትመንቱ ትልቁ መሠረት በመኾኑ የአምራቾችን ፍሰት እንዲጨምር ሚናው ጉልህ መኾኑን ታዝበና ብለዋል።
20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ክልል አቀፍ የማጠቃለያ መርሐ ግብር በደብረ ብርሃን ከተማ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
ዘጋቢ:- አበበች የኋላሸት
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
