አካታች ማኅበረሰብ በመገንባት አካል ጉዳተኞችን በልዩ ልዩ ጉዳዮች ተሳታፊ ማድረግ ይገባል።

6
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ”አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማኅበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማኅበራዊ እድገት” በሚል መሪ መልዕክት የአካል ጉዳተኞችን ቀን እየተከበረ ነው።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ እና የባሕር ዳር ከተማ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን በጋራ በመኾን ነው በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የአካል ጉዳተኞች ቀን እያከበሩ የሚገኙት።
የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ንጹህ ሽፈራው መንግሥት አካታች ማኅበረሰብ መገንባትን ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ሥራዎች እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በልማት ሥራዎች፣ በሥራ እድል ፈጠራ እና ሌሎች ተግባራት ላይ ባሕር ዳር ከተማ የተሻለ አፈጻጸም ያለው መኾኑን አንስተዋል። ቀሪ ሥራዎች ግን አሉ ብለዋል።
በቀጣይም በክልሉ በሚገኙ በሁሉም ዞኖች እና ከተማ አሥተዳደሮች አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ማኅበረሰብ በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተጠቃሚነታቸውን እና ተሳታፊነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ነው የገለጹት።
ማኅበረሰቡ፣ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት፣ የግል የልማት ድርጅቶች እና ራሳቸው አካል ጉዳተኞች ከአካል ጉዳተኞች አኳያ በሚሠሩ ተግባራት ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠት ተጀመረ።
Next articleየብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን የኢትዮጵያን ኅብረ ብሔራዊነት በሚያሳይ መልኩ እየተከበረ ነው።