የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው።

6
ደብረ ብርሃን: ኅዳር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ መልዕክት በአማራ ክልል ደረጃ የማጠቃለያ መርሐ ግብር በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በዓሉ በአማራ ክልል ከኅዳር አንድ ጀምሮ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ሲከበር ቆይቷል።
በበዓሉ አከባበር ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ የጨፌ ኦሮሚያ፣ የአፋር ክልል እና የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አፈ ጉባኤዎች እና የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleከችግር በመላቀቅ ወደ ተሟላ ሰላም ለመመለስ መምከር ይገባል።
Next articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከአልሚ ባለሃብቶች ጋር በባሕር ዳር ከተማ እየተወያዩ ነው።