
ደሴ: ኅዳር 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የጸጥታ መዋቅር መሪዎች በወቅታዊ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ በደሴ ከተማ ምክክር እያደረጉ ነው፡፡
በመድረኩ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል
ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የኾኑት ሌተናል ጀኔራል አሰፋ ቸኮል እናሌሎችም የክልል፣ የዞን እና የከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በአማራ ክልል ባለፉት ጊዜያት በሰላም፣ በልማት እና መልካም አሥተዳደር ዘርፎች የመጡ ለውጦችን ማስቀጠል እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
በውይይቱ በክልሉ ባለፉት ጊዜያት የነበሩ የሰላም፣ የልማት እና መልካም አሥተዳደር ሁኔታዎችን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎም ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
