ወልድያ ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና እየሰጠ ነው።

8

ወልድያ: ኅዳር 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በወልድያ ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።

ሕክምና አገልግሎት ያገኙ ታካሚዎች ዓይን ብርሃናቸውን በማጣታቸው ተቸግረው እንደኖሩ ነግረውናል። ተንቀሳቅሶ መሥራት የለመደ በሰው እጅ ላይ መውደቅ ሥነ ልቦናዊ ጉዳቱ ከባድ እንደነበር ነው ትውስታቸውን የገለጹልን። ታካሚዎቹ ለተሰጣቸው አገልግሎትም አመስግነዋል።

በሆስፒታሉ የዓይን ሕክምና ክፍል ኀላፊ ሲስተር ሙሉ ዳርጌ የዓይን ሞራ ግርዶሽ በአብዛኛው ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ችግር መኾኑን አስረድተዋል። ቢኾንም ግን በተለያየ መንገድ ዓይን ላይ በሚደርስ አደጋ ምክንያትም ሊከሰት ይችላል ነው ያሉት።

በሞራ ግርዶሽ የሚከሰት ዓይነ ስውርነትን መታከም ስለሚቻል ታማሚዎች ወደ ሕክምና ቦታ እንዲመጡ ይመከራል ብለዋል።

ሆስፒታሉ በመደበኛነት ከሚሰጠው የሕክምና አገልግሎት ባሻገር በዘመቻ ከኪዩር ብላይንድነስ ጋር በመተባባር በነጻ ሕክምና እየሰጠ መቆየቱን ኀላፊዋ ተናግረዋል።

የነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምናው ኅዳር 27/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ነው። በዘመቻው 1 ሺህ ለሚኾኑ ሰዎች ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት መታቀዱንም ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለአካል ጉዳተኞች ምቹ የኾነ ተቋም በመገባት አካታችነትን ማረጋገጥ ይገባል።
Next articleባለፉት ጊዜያት በሰላም፣ በልማትና መልካም አሥተዳደር ዘርፎች የመጡ ለውጦችን ማስቀጠል ይገባል።