ኢሠማኮ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ድምፅ በአፍሪካም ኾነ በዓለም አደባባይ እንዲሰማ እየሠራ ነው።

5

አዲስ አበባ: ኅዳር 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 37ኛው የዓለም አቀፉ የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ITUC) ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የዓለም አቀፉ የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ITUC) ምክር ቤት ስብሰባ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር በኢትዮጵያ እንዲካሄድ ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ITUC) እና ኦል ሰብ ሰሃራን አፍሪካ በጋራ እንዳዘጋጁት ተነግሯል።

ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ እያሳየችው ያለው ሁለንተናዊ እድገት ብዙ እድሎችን እያስገኘላት ነው ያሉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዳንኤል ተሬሳ ይህ ጉባኤ በአፍሪካ ምድር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መዘጋጀቱ ትልቅ እድል መኾኑን ገልጸዋል።

በሀገራችን ሠራተኞች መብትና ጥቅማቸው ተከብሮ ሥራዎችን እንዲሠሩ ሕጎች እና መመሪያዎችን በማውጣት እና ተፈፃሚነታቸውንም በማረጋገጥ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል።

አሁንም ምንም ችግር የለም ሳይኾን በሠራተኞች የሚነሱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን በመወያየት እና በመነጋገር ለሁሉም ምቹ በኾነ መንገድ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መኾኑን አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ኢሠማኮ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ድምፅ በአፍሪካም ኾነ በዓለም አደባባይ እንዲሰማና ችግሮቻቸው እንዲፈቱ በማድረግ ረገድ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ እንዳለ ገልጸዋል።

37ኛውን የዓለም አቀፍ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ ማስተናገዷ በጋራ የመሥራታችን ትልቅ ማሳያ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ በቀጣይም የሠራተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ሥራዎች እንደሚሠሩ አመላክተዋል።

37ኛው ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ምክንያት የሆነው ኢሠማኮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ተቀባይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎላ መምጣቱ ማሳያ መሆኑም በመድረኩ ተነግሯል።

በጉባኤው የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ታድመዋል።

ጉባዔው ከኅዳር 23 እስከ ኅዳር 25/2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይም ተገልጿል።

ዘጋቢ:- ሰለሞን አሰፌ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article‎የእርሻ ሥራን እስከ ምርት ስብሰባ ድረስ ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመጠቀም ማዘመን ያስፈልጋል።
Next articleአካል ጉዳተኞችን በሁሉም የልማት ዘርፎች ማሳተፍ ይገባል።