37ኛው የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ቀኑ እየታሰበ ነው።

17
ጎንደር: ኅዳር 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ”ተግዳሮቶችን በመቋቋም የኤች አይ ቪ ኤድስ ምላሽን ዘላቂነት እናረጋግጥ” በሚል መሪ መልዕክት ነው እየተከበረ የሚገኘው። በመርሐ ግብሩ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ተገኝተዋል።
በመርሐ ግብሩ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአባላዘር እና ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ኦፊሰር ደረበ ሙላው ባቀረቡት የመወያያ ጽሑፍ የበሽታው ሥርጭት አሳሳቢ መኾኑን አንስተዋል።
የኤች አይቪ ኤድስ ቀን እንደ ዞን መከበር ዋና አላማው ቫይረሱን ለመከላከል ብሎም ለማጥፋት በሚሠራው ሥራ የመንግሥት ሠራተኞች አጋዢ እንዲኾኑ ያለመ መኾኑንም አንስተዋል።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከ5 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ምርመራ አድርገው ቫይረሱ በደማቸው መኖሩ የተረጋገጠ መኾኑን እና በ2017 ዓ.ም 291 ሰዎች መድኃኒት የጀመሩ መኾናቸው ተነስቷል።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፓለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ካሳው ንጉሤ
እየተቀዛቀዘ የመጣውን በሽታውን የመከላከል ተግባር በማጠናከር የተያዘውን ቫይረሱን የማጥፋት ተግባር ለማሳካት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ በበኩላቸው የበሽታው ሥርጭት እንዳይባባስ ለማድረግ ኀላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
ማኅበረሰቡ በበሽታው እንዳይጠቃ ለማድረግ የሚያስችሉ የግንዛቤ ፈጠራ ትምህርቶች መጠናከር እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል።
ዘጋቢ: ዳንኤል ወርቄ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleሙስናን ለመከላከል የሁሉንም አካላት ትብብር ያስፈልጋል።
Next articleየፖሊስ አባላት ሰላም እና ደኅንነትን ከማስጠበቅ ባሻገር የልማት ሥራዎችን እያከናወኑ ነው።