ራሱን የጎቤ ክፍለ ጦር ሰጠኝ ባብል ብርጌድ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የሰላም ጥሪውን ተቀበለ።

72

ባሕር ዳር: ኅዳር 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ‎‎ራሱን የጎቤ ክፍለ ጦር ሰጠኝ ባብል ብርጌድ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የሰላም ጥሪውን ተቀብሎ ወደ ሕዝብ መመለሱ ተገልጿል።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ታጥቆ ሲንቀሳቀስ የነበረው እና በጌታለ የማታው የሚመራው ራሱን የጎቤ ክፍለ ጦር ሰጠኝ ባብል ብርጌድ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ሕዝብ እና መንግሥት ያቀረቡለትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ዘጠኝ የቡድን አባላትን ይዞ ወደ ሕዝብ ተመልሷል።

ቡድኑ ሲገባ አንድ ዲሽቃ፣ አንድ አርባ ጎራሽ እና አምስት ክላሽ መሳሪያ እንዲሁም አባላቱ እስከነ ሙሉ ትጥቃቸው በሰላማዊ መንገድ ነው የተመለሱት።

የቡድኑ መሪ አቶ ጌታለ የማታው መንግሥት የሕዝቡን ጥያቄዎች እንደሚፈታ በማመናቸው መመለሳቸውን ገልጾ ከመንግሥት እና ከሕዝብ ጎን በመሰለፍ ሌሎች ጫካ የሚኖሩ ወንድሞችንም ወደ ሰላም የሚመጡበት ሁኔታ ለማመቻቸት ዝግጁ መኾናቸውን መናገሩን ከክልሉየመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየደብረ ማርቆስ – ደብረ ኤሊያስ – ተምጫ እና ጭምት መገንጠያ – ጭምት ከተማ መንገድ ግንባታ ዳግም ተጀመረ።
Next articleበመደጋገፍ የማይቀረፍ ችግር የለም።