የኮሪደር ልማት ለጎንደር ከተማ ከውበትም በላይ ችግሮችን የፈታ ነው።

22

ጎንደር: ኅዳር 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ የከተማዋን ማስተር ፕላን ለመጠበቅ የሚያግዝ መኾኑን የከተማ አሥተዳደሩ ከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ አስታውቋል።

‎በጎንደር ከተማ እየተሠራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ሥራ አንደኛው ዙር ተጠናቅቆ ሁለተኛው ዙር በሂደት ላይ ይገኛል።

‎በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ሙሉጌታ ታደሰ ልማት ናፍቋት የቆየችው ጎንደር ከተማ አሁን ላይ ታሪካዊ የመናገሻ ከተማነቷን በሚያሳይ መልኩ እየለማች ትገኛለች ብለዋል።

በሕዝብ ድጋፍ እና ርብርብ የልማት ሥራው በሚፈለገው ልክ እየተሠራ መኾኑንም አቶ ሙሉጌታ አንስተዋል። በከተማዋ እየተሠራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የከተማዋን ውበት ከመጠበቅ ባለፈ በከተማዋ ፈታኝ ኾኖ የቆየውን የከተማ ማስተር ፕላን ለማስጠበቅ እንዳስቻለ ተናግረዋል።

‎ያነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የኮሪደር ልማት ሥራው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን እንዳስገኘ ገልጸዋል። ለአብነትም ከተማዋን ውብ ከማድረግ ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠርን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ዕድሎችን እንዳመጣም ጠቅሰዋል።

‎ከተማዋን ለመንገድ ጥበት በመዳረግ ውበቷን ደብቀው የቆዮ የመንገድ ሱቆች እና ሕገ ወጥ ግንባታዎች መነሳታቸው ለነዋሪዎች እፎይታን እንደሰጠም ነው የተናገሩት።

‎በጎንደር ከተማ የሚከናወነው የኮሪደር ልማት ሥራ
‎ተጠናክሮ እንዲቀጥል ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።

‎ዘጋቢ:- ተስፋየ ጋሹ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአማራ ባንክ ከታክስ በፊት 655 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ።
Next articleየደብረ ማርቆስ – ደብረ ኤሊያስ – ተምጫ እና ጭምት መገንጠያ – ጭምት ከተማ መንገድ ግንባታ ዳግም ተጀመረ።