
አዲስ አበባ: ኅዳር 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ትክክለኛ መረጃ ለማሠባሠብ ይረዳው ዘንድ ለሕዝቡ መረጃ ለመስጠት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ በጥቃቅን፣ አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ በሚሉ ዘርፎች ተከፍሎ እንደሚካሄድ በመግለጫው ተነስቷል።
የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ (ዶ.ር) በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አገልግሎቱ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ድርጅቶችን ቆጠራ እያካሄደ እና የተለያዩ መረጃዎችን እያሠባሠበ ነው ብለዋል።
ይህ የኢኮኖሚ ድርጅቶች መረጀ ስብሰባ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እና ደረጃ ለማወቅ የሚደረግ እንጂ ለሌላ አላማ የሚውል አለመኾኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
መረጃው የሀገሪቱን የአገልግሎት እና የምርት አቅም ለማወቅ ስለኾነ ዜጎች ለሚጠየቁት ጥያቄ ትክከለኛ መረጃ በመስጠት ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።
ዘጋቢ:- ረህመት አደም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
