የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የቻይና አፍሪካ ትብብር የማይተካ ሚና እንደሚኖረው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ፡፡

210

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 12/2012 ዓ.ም (አብመድ) የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ያለመ በቪዲዮ የታገዘ ውይይት ትናንት ሰኔ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ፣ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶክተር)፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል።

በውይይቱ የተሳተፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ወረርሽኙን ለመግታት በቻይናና በአፍሪካ መካከል የሚደረገው ትብብር ከምንጊዜውም በላይ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ቻይና የኮሮና ወረርሽኝን ለመግታት የተከተለችውን ስልት እና የተገኘውን ውጤትም አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ ወረርሽኙን ለመግታት እያደረገች ባለው እንቅስቃሴ የቻይና መንግሥት እና እንደ ጃክማ የመሳሰሉት የቻይና በለሀብቶች እያደረጉት ላለው ያልተቋረጠ ድጋፍ ምስጋና በማቅረብም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

ውይይቱ ወረረሽኝ በታዳጊ ሀገራት ኢከኖሚና ማኅበራዊ እንቅስቀሴ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመቋቋም የሚያስችል አቅጣጫ ለማስቀመጥ ወሳኝ መሆኑንም መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ገኘነው መረጃ ያመላክል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleየፊታችን እሑድ በቀኑ ፀሐይ ትጨልማለች! ብርሃንዎን እንዳያጡም ይጠንቀቁ!
Next articleየባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮሮናቫይረስ ምርመራ ጀመረ፡፡