ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) በተገኙበት ኢትዮጵያ የምታዘጋጀውን የኮፕ 32ን ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ውይይት ተካሄደ።

26

ባሕር ዳር: ኅዳር 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት ኢትዮጵያ የምታዘጋጀውን የኮፕ 32ን ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ውይይት ተካሂዷል።

ትናንትና የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝዳንት መሰየምን ተከትሎ ዛሬ ጠዋት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት የሚያስችል የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ሥብሠባ ተደርጓል።

ሥብሠባው ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ስታስተናግድ አካታች እና በሚገባ የተሰናዳ ጉባኤ እንድታሳካ ለማረጋገጥ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት እንደነበር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሰብልን በኮምባይነር መሠብሠብ ምን ለውጥ አመጣ?
Next articleበአዲስ አበባ የአዳዲስ ኤምባሲዎች መከፈት የመዲናዋን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት የሚያጠናክር ነው።