
ደብረማርቆስ: ኅዳር 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን የባሶ ሊበን ወረዳ ትርፍ አምራች ከኾኑት ወረዳዎች መካከል ተጠቃሽ ነው። በወረዳው ስንዴ፣ ሰሊጥ፣ ቦሎቄ እና ሌሎች ሰብሎች በስፋት ይመረታሉ።
አርሶ አደሮች የደረሱ ሰብሎቻቸውን በግብርና ሜካናይዜሽን በመሠብሠባቸው የምርት ብክነትን መቀነስም ችለዋል። ጥራት ያለው ምርት ለገበያ ለማቅረብ እንዳስቻላቸውም ገልጸዋል።
አርሶ አደሮቹ በክላስተር በማምረታቸው ከዚህ በፊት ያጋጥሟቸው የነበሩ ችግሮችን እንዳስቀረላቸውም አብራርተዋል።
በወረዳው 51 ሺህ ሄክታር መሬት በአርሶ አደሮች እየለማ እንደሚገኝ የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የባሶ ሊበን ወረዳ ተወካይ አስተዳዳሪ እና ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ስሜነህ አሞኘ አርሶ አደሮች የስንዴ ማጨጃ ማሽኖችን መጠቀማቸው ጉልበት እና ጊዜያቸውን እንደቆጠበላቸውም ተናግረዋል።
ጥራት ያለው ምርትን ለኢንዱስትሪዎች በማቅረብ ተጠቃሚ መኾን እንደቻሉም አስገንዝበዋል።
በአካባቢው የሚገኙ የዱቄት ፋብሪካዎች የአርሶ አደሮችን ምርት በግብዓትነት መጠቀም መቻላቸው ግብርናውን ከኢንዱስትሪውን ጋር ለማስተሳሰር ያስቻለ ስለመኾኑም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
