የባሕር ዳር ስታዲየም ለባሕር ዳር ከተማ ተጨማሪ ውበት ነው።

8
ባሕር ዳር: ኅዳር 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ መሪዎች የባሕር ዳር ዓለም ዓቀፍ ስታዲየምን እየጎበኙ ነው። ለጎብኝዎቹ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ተሻገር አዳሙ ገለጻ አድርገዋል።
በጉብኝቱ እየተሳተፉ አሚኮ ያገኛቸው አቶ ፈንታው በለጠ ስታዲየሙ በችግር ሳይቆም በዚህ ደረጃ ተገንብቶ በማየታቸው መደነቃቸውን ገልጸዋል። ትልቅ ኩራት እንደተሰማቸውም አስረድተዋል። ስታዲየሙ የሀገር አቀፍ ትኩረትን የሚስብ እና ለስፖርት ቱሪዝሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ገልጸዋል።
ስታዲየሙ ለባሕር ዳር ከተማ ተጨማሪ ውበት መኾኑንም ነው የተናገሩት። የከተማዋን ብሎም የክልሉን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ ተጨማሪ አቅም ስለመኾኑም አመላክተዋል። ስታዲየሙ ተደጋግሞ ቢጎበኝም የማይጠገብ ነው ብለዋል።
ሌላኛዋ አስተያየት ሰጭ ወይዘሮ በላይነሽ ሲሳይ ስተዲየሙ ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ዕድል ይዞ የመጣ እንደኾነ ጠቁመዋል። ለኢኮኖሚው ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ነው የተናገሩት።
የስታዲየሙ መጠናቀቅ በክልሉ የተጀመረውን ልማት ለማስቀጠል ትልቅ ማሳያ ስለመኾኑም ነው ያነሱት።
ዘጋቢ፦አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የፀጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ድምፅ እንዲሰማ ማሻሻያዎችን ያድርግ” ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Next articleሦስት ኢንዱስትሪዎችን የያዘው ኤም ኤስ ኤ ኢንዱስትሪ