የትጥቅ ትግል ሰላምን አያረጋግጥም።

13

ጎንደር: ኅዳር 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥን ታሳቢ ያደረገ እና በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።

‎የሀገርን ሰላም በማረጋገጥ ልማት የሚያፋጥንን ፓርቲ ከመቃወም ይልቅ መደገፍ አለብን ያሉት የውይይቱ ተሳታፊ እና የኢህአፓ ፓርቲ አባል ካሳ በለጠ ናቸው። እንደ ፓርቲ የሀገር ሰላም እንዲጠበቅ እና እድገት እንዲፋጠን በጋራ እንሠራለን ብለዋል።‎

የኅብር ኢትዮጵያ ፓርቲ የጎንደር ቅርንጫፍ አሥተባባሪ ‎መኮንን ብርሃን ተፎካካሪ ፓርቲዎች የተረጋጋ እና ፍትሐዊ ምርጫ ማስኬድ እንዲቻል ቅድሚያ የሰላሙን ሁኔታ ምቹ የማድረግ ሂደቱን ሊያግዙ ይገባል ብለዋል። የተረጋጋ እና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ችግሮችን ለቅመን አውጥተን የጋራ ማድረግ መቻል አለብን ነው ያሉት።

‎ሕዝቡ ሰላምን የሚያናጉ አካላትን ሊያርም ይገባል ያሉት ደግሞ ከአገው ሸንጎ ፓርቲ ተሳታፊ ነጋ መርሻ ናቸው። የትጥቅ ትግል ሰላምን እንደማያረጋግጥም አስረድተዋል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ፋሲል ሰንደቁ የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ቢኖረንም የሀገራችን የሰላም ጉዳይ የጋራ ሊያደርገን ይገባል ብለዋል።

በጋራ መምከራችን የሠለጠነ የፖለቲካ አካሔዳችንን የሚያሳይ ነው ያሉት ኀላፊው ስለ ሀገራችን ሰላም፣ ልማት፣ እድገት እና ሉዓላዊነት በጋራ መሥራት አለብን ነው ያሉት።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ መኮንን ሰላምን ለማምጣት ዋጋ መክፈልን ይጠይቃል ብለዋል።

ተባብረን የጀመርነውን ልማት ማስቀጠል ከቻልን ሰላምን ማረጋገጥ እንችላለን ነው ያሉት።

የፖለቲካ ፓርቲዎች 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሐዊ እና ግልጸኝነት የተሞላበት እንዲኾን ቅድሚያ ሰላምን ማረጋገጥ ላይ በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባም ተመላክቷል።

‎ሥልጡን የፖለቲካ ሥርዓት መገንባት እንደሚገባም በውይይት መድረኩ ተመላክቷል።

ዘጋቢ:- ተስፋዬ ጋሹ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየነቀምት – አጋምሳ – ቡሬ የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት አፈጻጸም ከ63 በመቶ በላይ ደርሷል።
Next article“የሰላም ጥሪውን ተቀብለው የገቡት ዘግይተውም ቢኾን እውነታውን የተረዱት ናቸው” እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር)