የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮሮናቫይረስ ምርመራ ጀመረ፡፡

630

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 12/2012 ዓ.ም (አብመድ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጥበብ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ጀምሯል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኃላፊ የሺጌታ ገላው (ዶክተር) ለአብመድ እንዳሉት ጥበብ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀን 96 ናሙናዎችን መርመር የሚያስችል ላቦራቶሪ ሥራ ጀምሯል፡፡ በሆስፒታሉ አንድ የመመርመሪያ ማሽን እንዳለና ወደፊት ተጨማሪ ለማምጣት እንቅስቃሴ እንደተጀመረም አስታውቀዋል፡፡

በአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ ዳይሬክተር ማንአምኖት አገኝ እንደተናገሩት የጥበበ ግዮን ስፔሻላዝድ ሆስፒታል ምርመራ መጀመሩን ተከትሎ በክልሉ ስድስተኛው የናሙና መመርመሪያ ሆኗል፡፡ የክልሉን የምርመራ አቅም ከፍ እንደሚያደርገውም ገልጸዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ወልዲያ ላይ ምርመራ በቅርብ እንደሚጀመርም አስታውቀዋል፡፡ በቅርቡ በክልሉ በቀን እስከ 1 ሺህ 500 ናሙናዎችን ለመርመር እየተሠራ መሆኑን የተናገሩት አቶ ማንአምኖት “መተማ ላይ ለማስጀመር እንቅስቃሴ ተጀምሯል” ብለዋል፤ ነገር ግን ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል አመላክተዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleምሥራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ ወረራ ስጋት ተደቅኖበታል፡፡
Next articleየቀድሞ የአማራ ክልል መሪዎች የመታሰቢያ የፓናል ውይይት በደብረ ታቦር እየተካሄደ ነው፡፡