
ባሕር ዳር: ኅዳር 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአቡዳቢ ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ ካሌድ ቢን መሐሙድ ቢን ዛይድ አልናህያን ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን የአቡዳቢ ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ ካሌድ ቢን መሐሙድ ቢን ዛይድ አልናህያን ጋር የመወያየት እድል አግኝተናል ብለዋል።
ውይይታችን ስትራቴጂካዊ ትብብራችንን በማጠናከር ለበለጠ የጋራ ርምጃ እድሎችን መመልከት ላይ ያተኮረ ነበር ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
