
ባሕር ዳር: ኅዳር 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአይ ኤም ኤፍ ፕሬዝዳንት ክሪስታሊና ጂኦርጂየቫ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባኤ ጎን ለጎን ከአይ ኤም ኤፍ (IMF) ፕሬዝዳንት ክሪስታሊና ጂኦርጂየቫ ጋር በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያዎች ፣ በሀገራችን የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ ዘላቂ እና አካታች እድገትን ለመደገፍ ትብብራችንን ለማጠናከር ስላሉ እድሎች ላይ ተወያይተናል ብለዋል።
ለአይ ኤም ኤፍ የዘለቀ ግንኙነት ምስጋናዬን እያቀረብኩ የጋራ ትኩረቶቻችንን ለመፈፀም መነሳታችንንም እገልጻለሁ ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
