
ባሕር ዳር: ኅዳር 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ዋዜማ የአስተናጋጃችን ሀገር ፕሬዝደንት ከኾኑት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተገናኝተናል ብለዋል።
ታሪካዊው የቡድን 20 ጉባኤ በአፍሪካ ምድር እንደመሰናዳቱ በተለያዩ ጉዳዮች፣ በጉባኤው የአፍሪካ የወል ድምጽ እና የጋራ ፍላጎት የሚቀርብበትን ሁኔታ ተወያይተናል ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
