የመንግሥት ሠራተኞች በተሰማሩበት የሥራ መስክ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት አለባቸው።

3
ወልድያ: ኅዳር 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የወልድያ ከተማ አሥተዳደር “አገልጋይ እና የሰላም ዘብ የመንግሥት ሠራተኛ ለሁለንተናዊ እመርታ” በሚል መሪ መልዕክት ከመምሪያ እና ክፍለ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ጋር ምክክር አካሂዷል።
የምክክሩ ተሳታፊ የመንግሥት ሠራተኞች በአንዳንድ ተቋማት ተገልጋዮች አላስፈላጊ መጉላላት ሲደርስባቸው ይስተዋላል ብለዋል።
በተለይም በሥራ ሰዓት ጉድለት እና በአላስፈላጊ ቀጠሮ በፍጥነት ሊሠሩ የሚገቡ ተግባራት ይጓተታሉ ነው ያሉት። በዚህም የተገልጋዮችን ምሬት እንደሚያጎላ ገልጸዋል።
የመንግሥት ሠራተኞች በተሰማሩበት የሥራ መስክ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸውም ተናግረዋል።
የተገልጋዮችን ርካታ ማሳደግ አኩራፊ እንዳይኖር ሚናው ጉልህ መኾኑን የጠቀሱት ተሳታፊዎቹ የተረጋጋ ከተማ ለማፅናት እና የመንግሥትን ቅቡልነት ለማረጋገጥ በትጋት መሥራት እንደሚገባም ገልጸዋል።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ተነሳሽነት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል።
የመንግሥት ሠራተኞችን የሥራ ትጋት እና የአገልግሎት ጥራት ለማሳደግ ከተማ አሥተዳደሩ አስፈላጊውን ክትትል እና ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
በከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ጉድለት የሚፈፅሙ ባለሙያዎች ላይ የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድም አመላክተዋል።
አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleማኅበረሰቡን በቅንነት እና በግልጸኝነት ለማገልገል ጠንክረው እንደሚሠሩ የምዕራብ ጎንደር ዞን የመንግሥት ሠራተኞች ተናገሩ።
Next articleበ78 ዓመት እንደ ወጣት….