
ባሕር ዳር: ኅዳር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የማሌዢያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂምን የኢትዮጵያ ቆይታ በተለያዩ ዘርፎች ስምምነት የተደረሰበት ፍሬያማ ቆይታ እንደነበር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በኢትዮጵያ የሦሥት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደረጉትን የማሌዢያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂምን ወደ ሀገራቸው ሸኝተናል ብለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ቆይታ በሁለትዮሽ የጋራ አጀንዳዎች ላይ ውይይት የተካሄደበት እና በተለያዩ ዘርፎች ስምምነት የተደረሰበት ፍሬያማ ቆይታ ነበር ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
