አርቶ ፍልውኃ የተፈጥሮ ስቲም

3

አዲስ አበባ: ኅዳር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ካሉ ተፈጥሮአዊ የቱሪስት መስህቦች አንዱ የኾነው የአርቶ ፍል ውኃ በሀላባ ዞን በዌራ ወረዳ ታችኛው አርሾ ቀበሌ ይገኛል።

አርቶ ፍልውኃ ከመስህብነቱ ባለፈ በፈዋሽነቱም ይታወቃል።ከዋና ከተማዋ ሀላባ ቁሊቶ 10 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የሚገኝ ቦታ ነው።

የሀላባ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኀላፊ ሀሩና አህመድ በዞኑ ካሉት የቱሪስት መዳረሻዎች አንዱ የኾነው የተፈጥሮ ስቲም አርቶ ፍልውኃ ከመስህብነቱ ባለፈ ለአካባቢው ማኅበረሰብ የፈውስ ምንጭ ኾኖ እያገለገለ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የአካባቢው ማኅበረሰብ ለመስኖ ልማት እና ለመዝናኛነት እየተጠቀመበት መኾኑንም ገልጸዋል።

አካባቢውን በመሠረተ ልማት ተደራሽ በማድረግ ምቹ የጤና ቱሪዝም መዳረሻ የማድረግ ሥራ እየተሠራ መኾኑንም ጠቁመዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎችም በፈዋሽነቱ የሚታወቀውን የአርቶ ፍልውኃ ለምግብ ማብሰል፣ እንፋሎቱን ለመታጠን እና ለመስኖ ልማት እንደሚጠቀሙበት ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ በአካባቢው የመሠረተ ልማት፣ የማረፊያ እና የመስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ባለመኖራቸው መቸገራቸውንም ተናግረዋል።

የዞኑ አሥተዳደርም አካባቢውን ለማልማት “አርቶ ፋማ” የሚል ፕሮጀክት ቀርፆ ወደ ሥራ መግባቱን እና ለዚያ የሚያግዝም የዲዛይን ሥራ ማጠናቀቁን ገልጿል።

የአርቶ ፍልውኃ ተፈጥሮአዊ ይዘቱ ዐይን የሚስብ ገፅታን የተላበሰ ነው። ዙሪያውን በበርካታ የዕፅዋት ዝርያዎች፣ በዱር እንሰሳት እና በአዕዋፋት የተከበበ ነው።

ዘጋቢ፦ ቤተልሔም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአማራጭ የሙግት መፍቻ ሥርዓቶችን በማጠናከር የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው።
Next articleኀላፊነትን አውቆ መሥራት ካልተቻለ የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን መቅረፍ አይቻልም።