አማራጭ የሙግት መፍቻ ሥርዓቶችን በማጠናከር የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው።

3

ደባርቅ: ኅዳር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ‎‎የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተቀናጀ የአሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሠራ መኾኑን ገልጿል።

የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ግዛቸው ሙጬ የዳኝነት ሥርዓቱን ለማሻሻል እና በቴክኖሎጂ ለማገዝ እየተሠራ ነው ብለዋል።

የኢ-ፋይሊንግ አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች የዲጂታላይዜሽን አማራጮችን እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የሰው ኀይሉን በሥልጠና እና በሌሎች የአቅም ማጓልበቻ አማራጮች የማብቃት ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

አማራጭ የሙግት መፍቻ ሥርዓቶችን በማጠናከር የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በዚህም የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሥርዓቶችን ወደ ሥራ የማስገባት ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዳኞች አሥተዳደር ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አማረ መኮንን የዳኞችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ሕጻናት እና ሴቶችን ጨምሮ ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ የልዩ ችሎት የዳኝነት ሥርዓቶችን የማስጀመር ተግባር እየተከናዎነ ነው ብለዋል።

በማሳያነትም በደባርቅ ወረዳ ፍርድ ቤት መጀመሩን እና ውጤታማ አገልግሎት እየተሰጠ መኾኑን አንስተዋል።

የተቀናጀ የአሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሠራ እንደኾነም ጠቁመዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢንዱስትሪውን የማምረት አቅም በ2018 በጀት ዓመት 63 በመቶ ለማድረስ ታቅዷል፡፡
Next articleአርቶ ፍልውኃ የተፈጥሮ ስቲም