
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 1 2/2012 ዓ.ም (አብመድ) ዴክሳሜታሶንን እንደ ድንገተኛ ሕክምና ለመጠቀም መወሰኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቀዋል።
መድኃኒቱን በተመለከተ በእንግሊዝ መንግሥት የተካሔደውን ጥናት እና ሪፖርት ጤና ሚኒስቴር በዝርዝር ማየቱን ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገጻቸው ገልጸዋል።
ከሕክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድን እና ከጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት የተሰጠውን ምክረ ሐሳብ መሠረት በማድረግም ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮሮናቫይረስ ሕሙማን አነስተኛ መጠን ያለው ዴክሳሜታዞን እንደ ድንገተኛ ሕክምና ለመጠቀም መወሰኑን ነው ዶክተር ሊያ ያስታወቁት፡፡
ሕክምናውን አስመልክቶ ዝርዝር መመሪያ በቅርቡ እንደሚወጣም ጤና ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት መድኃኒቱን በተመለከተ ከእንግሊዝ ተመራማሪዎች የቀረበውን ሀሳብ በአወንታ መመልከቱን መግለጹ ይታወሳል፡፡
በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለመደረግ ግን የጤና ሚኒስቴርን ውሳኔ ማግኘት እንደሚገባ አብመድ ያነጋገራቸው የህክምና ባለሙያዎች መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡
