የክልሉን ሰላም ለማጽናት በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቃል።

3

ጎንደር: ኅዳር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለጎንደር ቀጣና ፖሊስ መሪዎች እና አባላት የሪፎርም አፈጻጸም እና የአመራር አቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠ ነው።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አወቀ አስፈሬ ለተገኘው አንጻራዊ ሰላም የፖሊስ እና የጸጥታ አባላት እየተወጡት ላለው ተግባር ምስጋና አቅርበዋል። ሰላምን ለማጽናት በቀጣይም የጸጥታ አካላት በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ለለውጥ ራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል ብለዋል። ሪፎርም አዳዲስ ለውጦች የሚያመጣ እና የሚተገብር በመኾኑ ለለውጥ ዝግጁ መኾን፣ መቀበል እና መተግበር ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ዓለም እየተቀያየረ ካለበት የወንጀል ታሪክ ውስጥ አቅምን በማሳደግ እና ከሚፈጸሙ ወንጀሎች በላይ በመኾን ቀድሞ የሚከላከል አቅም ሊኖረን ይገባል ብለዋል።

የአካባቢውን አንጻራዊ ሰላም ለማስጠበቅ እና የክልሉን ሰላም ለማጽናት በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚያገባም ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የአሥተዳደር እና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ ሥልጠናው የሪፎርም ትግበራ አፈጻጸም የሚገመገምበት መኾኑን ተናግረዋል። በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር የሪፎርም ለውጥ እንዲደረግ መነሻ መኾኑንም አስታውሰዋል።

በሪፎርሙ የተለያዩ እክሎች ቢፈጠሩም የክልሉ መንግሥት እና የሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት በወሰዱት ቁርጠኝነት እየተተገበረ ይገኛል ነው ያሉት።

በተቋሙ የሰው ኃይል አደረጃጀቱን ለማዘመን ፣ የአሠራር ሥርዓቱን ቀልጣፋ ለማድረግ፣ ዘላቂ እና ፍትሐዊ መዋቅርን ለማደራጀት መሠራቱን ተናግረዋል።

በሥልጠናው በሪፎርሙ የታዩ ለውጦችን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የምንመለከትበት ነው ብለዋል። ሥልጠናው ሁሉም የየራሱን ድርሻ እና ኀላፊነት አውቆ የሚተገበርበት መኾኑንም ተናግረዋል።

ዘጋቢ :- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየፖሊስ ዋና ሥራው ሰብዓዊ መብትን ማክበር እና ማስከበር ነው።
Next articleበሰው ሠራሽ አስተውሎት የምርምር እና ልማት ልኅቀት ማዕከል የመኾን ራዕይን የሰነቀ ተቋም።