የሮዝመሪ ምርትን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከ4 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማግኘቱን የስልጤ ዞን ገለጸ።

3

አዲስ አበባ: ኅዳር 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ)

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኀላፊ ሙበራ ከማል በዞኑ ከ8ሺህ 200 ሄክታር በላይ መሬት በሮዝመሪ ምርት እየለማ ነው ብለዋል።

 

ዞኑ ጥራት ያላቸው የሮዝመሪ ምርቶች ከማዕከል አልፎ ለውጭ ገበያ እያቀረበ መኾኑንም ገልጸዋል።

 

ለዚህ እንዲያግዝም ምርት ከአርሶአደሮች እየሠበሠቡ ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ማኅበሮችን የማደራጀት ሥራ ተሠርቷል ብለዋል። በዚህም የእሴት ሰንሰለቱን ጠብቆ ለገበያ እንዲቀርብ እየተደረገ ነው።

 

ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ ከ103ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ተመርቶ 31ሺ 300 ኩንታሉን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከ4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት መቻሉንም ገልጸዋል።

 

በዞኑ ወራቤ ከተማ አሥተዳደር የአንሸቤሶ ቀበሌ አርሶአደሮች አካባቢው ላይ ከዚህ ቀደም ይታወቅ የነበረውን የባሕር ዛፍ ተክል በማሰወገድ እና በሮዝመሪ በመተካት ኑሮአቸው እየተሻሻለ እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውም እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

 

የሮዝመሪ ምርት አሲዳማ መሬቶችን ለማከምም ጠቀሜታው የጎላ እንደኾነም ተገልጿል።

 

ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከ46 ወደ 59 ነጥብ 2 በመቶ አድጓል። 
Next articleበአዕምሮ እና በአካል የጠነከረ ትውልድን ለመገንባት የሕፃናትን መብቶች ማክበር ይገባል።