ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ሠመራ ሎጊያ ከተማ ገብተዋል።

5

ባሕር ዳር: ኅዳር 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የምድረ ቀደምትነታችን ሕያው ምስክርና የሰው ዘር መገኛ፣ የኤርታሌ እሳተ ገሞራና የዳሎል ድንቅ ገጸ ምድር ባለቤት፣ የተፈጥሮና የባሕል ሀብታም ወደኾነችው የአፋሮች ውብ ከተማ ሠመራ ሎጊያ ገብተናል ብለዋል።

በሠመራ ሡልጣን ዓሊሚራህ ሐንፋሬ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ላደረጉልን የአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር፣ ለክልሉ ከፍተኛ መሪዎች ፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለሠመራ ከተማ ነዋሪዎች ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ነው ያሉት።

በቆይታቸው በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚመለከቱም ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየባሕላዊ ሽምግልና ሥርዓት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
Next articleትክክለኛ ግብር ካልተሰበሰበ ልማት ማልማት አይቻልም።