
አዲስ አበባ: ኅዳር 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የስልጤ ዞን የአካባቢውን ማኅበረሰብ ባሕል፣ ታሪክ እና ትውፊት በውስጡ የያዘውን የስልጤ ዞን የባሕል ሙዚየም በየዓመቱ ከ15 ሺህ በላይ ጎብኝዎች ይጎበኙታል።
ግንባታው በ1999 ዓ.ም ተጀምሮ በ2003 ዓ.ም የተጠናቀቀው ሙዚየሙ በውስጡ በአፍሪካ ድንቃድንቅ የተመዘገበውን 1ሜትር ከ20 ሴንቲሜትር ርዝማኔ ያለውን ከእንጨት የተሠራ ጫማን ጨምሮ 500 ቅርሶችን በውስጡ አቅፎ ይዟል።
የስልጤ ዞን ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ ይርዳው ናስር (ዶ.ር) ሙዚየሙ 24 ሺህ ካሬ መሬት ላይ ያረፈ ነው ብለዋል።
በውስጡም የስልጤ ማኅበረሰብ ይጠቀምባቸው የነበሩ ሃይማኖታዊ መጽሐፎች፣ ጥንታዊ የቤት ውስጥ መገልገያ እና የእርሻ መሳሪያዎች፣ ባሕላዊ አልባሳት እና የሙዚቃ መሳሪያዎችን እንደያዘ ገልጸዋል።
የዞኑ የሀገር በቀል የግጭት አፈታት ሥርዓቱን ጨምሮ አጠቃላይ በሙዚየሙ ያሉ ቅርሶችን ለማስተዋወቅ እየተሠራ ነውም ብለዋል።
በተለይም በክልሉ የሚከበረውን 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ለማክበር ወደ አካባቢው የሚመጡ ጎብኝዎችን ለመቀበል ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
