“የብልጽግና ጉዟችን ሁሉንም ማኅበረሰብ ተጠቃሚ በማድረግ ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ራዕይ የሚመራ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

4

ባሕር ዳር: ኅዳር 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት መንግሥት ለሰው ተኮር አጀንዳዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ለአካታች ልማት እየሠራ ነው ብለዋል።

በደሴ ከተማ የተመለከትናቸው የግብርና፣ የኢንዱስትሪ ምርት ግብይት ማዕከል እና የእንጀራ መጋገራሪያ አዳራሽ ሥራዎች የሕዝባችንን የየዕለት ችግሮች ለመፍታት ለምናደርገው ጥረት ማሳያዎች ናቸው ነው ያሉት።

የግብይት ማዕከሉ ዋና ዓላማ አምራቾች እና ሸማቾችን በማገናኘት እና በመካከል ያለውን የተንዛዛ የግብይት ሰንሰለት በማሳጠር ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን ማረጋጋት ነው ብለዋል።

ማዕከሉ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን እና የእንስሳት ተዋጽኦዎች ግብይት እንደሚካሄድበት ገልጸዋል።

የደሴ ከተማ የቧንቧ ውሃ የእንጀራ መጋገራሪያ አዳራሽ ግንባታ እንጀራ በመጋገር ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠርና ምርታማነትን በማስፋፋት የዜጎች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥን ዓላማ ያደረገ መኾኑን አመላክተዋል።

የብልጽግና ጉዟችን ሁሉንም ማኅበረሰብ ተጠቃሚ በማድረግ ማኅበራዊ ፍትሕን ያረጋገጠ ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ራዕይ የሚመራ ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየደቡብ ወሎ ዞን ያሠለጠናቸውን የሰላም አስከባሪ አባላትን በጊምባ ከተማ አስመረቀ።
Next articleየልማት ሥራዎችን ለመሥራት ግብርን በወቅቱ እና በአግባቡ መሠብሠብ አስፈላጊ ነው።