በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ሦስት ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፡፡

446

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 09/2012 ዓ.ም (አብመድ) በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 662 የላቦራቶሪ ምርመራ በ ሦስት ሰዎች ላይ ቫይረሱ መኖሩ ተረጋግጧል፡፡

ቫይረሱ እንዳለባቸው በምርመራ የተረጋገጡትም አንድ ከመተማ ለይቶ ማቆያ፣ አንድ ከወረታ እና አንድ ደግሞ ከተሁለደሬ ናቸው፡፡ በምርመራ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጡት ከ 32 እስከ 70 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሁለት ወንዶች እና አንድ ሴት ናቸው፡፡

በአማራ ክልል እስከ ዛሬ ሰኔ 9/2012 ዓ.ም ድረስ ለ 6 ሺህ 252 ሰዎች የናሙና ምርመራ ተደርጎ በ 234 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡ በ24 ሰዓታት ውስጥ በአማራ ክልል በአዲስ ያገገመም ሆነ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቱ ያለፈ ሰው የለም፡፡

በክልሉ በጽኑ ህሙማን የህክምና ክፍል ውስጥ የገባ ታማሚ አለመኖሩን እና ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከከላት ውስጥ የሚገኙት ሁሉም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ነው ቢሮው ያስታወቀው፡፡

በደጀኔ በቀለ

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleበኢትዮጵያ ተጨማሪ 109 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ የአንድ ሰው ሕይወትም አልፏል፡፡
Next articleባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችሉ የፈጠራ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡