የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማት ስኬታማ ሥራዎችን መሥራቱን የምሥራቅ ጉራጌ ዞን አስታወቀ።

2
አዲስ አበባ: ኅዳር 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዞኑ ያለውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው አልሚዎች በተለያዩ ዘርፎች እንዲሠማሩ የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ጥሪ አቅርቧል።
የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ሙስጠፋ ሀሰን ዞኑ ከተመሠረተ አጭር ጊዜ ቢኾንም በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
በግብርናው ዘርፍ ትልቅ አቅም ያለው እና ትርፍ አምራች በመኾኑ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርጉ እና የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች መሠራታቸውን ነው የገለጹት።
የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ስኬታማ ሥራዎች መከናወናቸውንም አንስተዋል።
በሦስት ምዕራፍ በሚሠሩ የኮሪደር ልማት እና አስጊ የነበሩ የወንዝ ዳር አካባቢዎችን በማልማትም ተሞክሮ የሚወሰድበት 42 ሄክታር መሬት የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ ልማት ተሠርቶ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅም ጠቁመዋል።
በዞኑ ባለው የጥሬቃ አቅርቦት እና ተፈላጊ የሰው ኃይል ምክንያት አካባቢውን መርጠው በተለያዩ ዘርፎች የሀገር ውስጥ እና የውጭ ባለሀብቶች ግዙፍ ፍብሪካዎችን ገንብተው ወደ ሥራ እየገቡ መኾኑን ነው የተናገሩት።
ዞኑ ያሉትን ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም የአካባቢው ተወላጅ አልሚዎች ወደ ዞኑ መጥተው እንዲሠማሩም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ቤተልሔም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article‎ሕጻናት የሀገር የወደፊት ተስፋ እና ሃብት ናቸው።
Next articleየኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ብቃት ያለው የጸጥታ ኃይል መገንባት ያስፈልጋል።