ለፖሊስ አባላት የተሰጠው ዕውቅና እና ማበረታቻ የበለጠ ለሥራ የሚያነሳሳ ነው።

4
ጎንደር: ኅዳር 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ጀብድ ለፈጸሙ እና
የላቀ ሥራ ላስመዘገቡ የፖሊስ አባላት የማዕረግ፣ የእርከን፣ የሰርቲፊኬት ማበረታቻ እና የዕውቅና ሽልማት ሰጥቷል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው የፖሊስ አባላት ሀገር ሰላም እንድትኾን መስዋዕትነት እየከፈሉ መኾናቸውን ተናግረዋል።
ከሕዝብ የተሰጣቸውን ኀላፊነት በጀግንነት ለተወጡ የፖሊስ አባላት ዕውቅና መስጠት እና መዘከር እንደሚገባም ገልጸዋል።
ለፖሊስ አባላት የተሰጠው ዕውቅና እና ማበረታቻ አባላቱ የበለጠ ሥራ እንዲሠሩ የሚያግዝ መኾኑን የገለጹት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በቀጣይ በከተማ አሥተዳደሩ የሚከበሩ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ የራሳቸውን ኀላፊነት እንዲወጡም አሳስበዋል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስ አሁን ላይ የሰላም ማስከበር ሥራን በሚገባ ለማረጋገጥ የፖሊስ አባላት ኀላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ እየተወጡ መኾናቸውን ገልጸዋል።
የተጀመረውን ሰላም የማስከበር እና የሪፎርም ተግባር ለማስቀጠል በጋራ መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል።
እውቅና የተሰጣቸው የፖሊስ አባላትም የተሰጣቸው ዕውቅና ከማኅበረሰቡ ጋር በጋራ በመሥራታቸው ያገኙት መኾኑን አንስተዋል።
የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ ከፖሊስ አካላት በተጨማሪ ማኅበረሰቡ እገዛ እያደረገ መኾኑን ተናግረዋል። የፖሊስ አባላት የተሰጣቸው ዕውቅና ለቀጣይ ሥራቸው መነሳሳትን የሚፈጥር መኾኑን አመላክተዋል።
የተሰጣቸውን የሕዝብ አደራ ጠብቀው ሰላምን ለማስፈን በትኩረት እንደሚሠሩም ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፦ ደስታ ካሳ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleአሚኮ ከዘገባ ሥራዎች ባለፈ የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር እየሠራ ነው።
Next article‎ሕጻናት የሀገር የወደፊት ተስፋ እና ሃብት ናቸው።