የተዘረጋው አሠራር ፈጣን እና ዘመናዊ በመኾኑ የመንግሥት አገልግሎቱን በቀላሉ ለማግኘት ያስችላል።

1

ደብረ ማርቆስ: ኅዳር 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አዲሱን የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የቀጥታ ኦን ላይን ምዝገባ ማስጀመር መርሐግብር ተካሂዷል።

በከተማው መንቆረር ክፍለ ከተማ ተገኝተው የመርሐ ግብሩን መጀመር አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የደብረ ማርቆስ ከተማ ምክትል ከንቲባ ስለሽ ተመስገን የዜጎችን ሕጋዊ መብት እና ማንነት ለማስከበር የመረጃ አያያዝ ሥርዓትን በዘመናዊ መንገድ መያዝ አስፈላጊ መኾኑን ገልጸዋል።
የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የዜጎችን መረጃ ጥራት እና ተአማኒነት በማረጋገጥ ተገልጋዮች በቴክኖሎጅ የታገዘ የተደራጀ አገልግሎት እንዲያገኙ ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል።
የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ መረጃን መሠረት ያደረገ ውሳኔ ለመስጠት ፋይዳው የጎላ በመኾኑ ማኅበረሰቡ ሁነቶችን በወቅቱ በማስመዝገብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲኾን ምክትል ከንቲባው አሳስበዋል።
የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ሲያካሂዱ አሚኮ ያገኛቸው ተገልጋዮችም የተዘረጋው አሠራር ፈጣን እና ዘመናዊ በመኾኑ አገልግሎቱን በቀላሉ ለማግኘት እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።
የከተማው ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ተወካይ ኀላፊ ትዕግስት ልየው በቀድሞው አጠራሩ ወሳኝ ኩነት፣ በአሁኑ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ በአዋጅ ተሻሽሎ በአደገ ቴክሎጂ የሰው ሃብት መረጃን አሟልቶ ለመያዝ ከወረቀት አሠራር ወጥቶ የቀጥታ ኦን ላይን የአሠራር ሥርዓት ተቀርጾለት ወደ ሥራ መግባቱን አብራርተዋል።
ተወካይ ኀላፊዋ ትዕግስት ልየው በከተማው ሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተገልጋዩ የተቀላጠፈ አገልግሎት እየተሰጠ መኾኑንም ገልጸዋል።
የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ውጤታማ እንዲኾን የሁሉንም ቅንጂታዊ አሠራር የሚጠይቅ መኾኑም ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየማርበርግ በሽታን ለመቆጣጠር ልዩ ክትትል እየተደረገ መኾኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
Next articleመሶብ የአንድ አገልግሎት ማዕከል ዜጎች ክብራቸው ተጠብቆ እና ሳይንገላቱ ተጠቃሚ እንዲኾኑ የሚያስችል ነው።