ሁለንተናዊ ብዝኀነትን ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት መጠቀም ይገባል።

2
ጎንደር: ኅዳር 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 20ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን እየተከበረ ነው።
ቀኑን አስመልክቶ በዞኑ ከሚገኙ መንግሥት ሠራተኞች ጋር የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ አላምረው አበራ ሁለንተናዊ ብዝኀነትን ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት መጠቀም ይገባል ብለዋል። ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ብዝኀ ሀብት መኾኑንም ገልጸዋል።
የጋራ ተጠቃሚነትን እና አንድነትን የሚያጎለብቱ እሴቶች ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ እና ለዴሞክራሲዊ ሥርዓት ተግባራዊነት ወሳኝ ሚና እንዳላቸውም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ያላትን ብዝኀነት ለመልካም ተግባራት መጠቀም አስፈላጊ መኾኑንም ገልጸዋል።
ባለፉት ዓመታትም ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ተጠናክሮ መዝለቁን አመላክተዋል። እለቱ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ፅንሰ ሀሳብን ለማስረፅ እና በጋራ ለመኖር የሚያስችል ውይይት የሚደረግበት መኾኑን ተናግረዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ የመንግሥት ሠራተኞች ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት አበርክቶው የጎላ መኾኑን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በብዝኀነት የደመቀች መኾኗን የገለጹት ተሳታፊዎች አንድ ኾኖ በመቆም ለሀገር ሰላም፣ ልማት እና ዴሞክራሲያዊ ግንባታ መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ቃልኪዳን ኃይሌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleየአፈር ለምነትን እና ምርታማነትን ለማሻሻል ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው።
Next articleየማርበርግ በሽታን ለመቆጣጠር ልዩ ክትትል እየተደረገ መኾኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።